Tuesday, August 13, 2013

Celebrating Buhe (The Transfiguration)

Hoya Hoye
Buhe is one of the many religious celebrations that the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church celebrates annually to commemorate the day Jesus took his three disciples to the high mountain. Prior to taking his disciples to the mountain, he has asked them a simple question, “Who do people say the Son of Man is? They replied, “Some say John the Baptist; others say Elijah; and still others, Jeremiah or one of the prophets.”  Jesus continued and asked his disciples “ who do you say I am?” One of the disciples, Simon Peter said, ““You are the Messiah, the Son of the living God.”

The reason that Jesus took his disciples to the mountain is so his disciples can get a crystal clear answer to Who Jesus is. The transfiguration reveled that Jesus is not Mosses nor is he Elijah or any of the prophets, but The Alpha and Omega. .



The songs that we, Ethiopians sing in Buhe's day is as follow

የቡሄ በዓል ትልቅ ታሪክ አለው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ደግሞ «ደብረታቦር» እየተባለ ይጠራል፡፡ በየዓመቱ ነሐሴ አሥራ ሦስት ቀን ይከበራል፡

ቡሄ በሉ (2)
ያዳም ልጅ ሁሉ
የእኛማ ጌታ የዓለም ፈጣሪ
የሰላም አምላክ ትሁት መሀሪ
በደብረታቦር የተገለጸው
ልብሱ እንደ ብርሀን ያንጸባረቀው

ድምጽህን ሰማና በብሩህ ደመና (2
የቡሄው ብርሀን ለእኛ መጣልን (2)

ያዕቆብ ዮሃንስ ! እንዲሁም ጴጥሮስ
አምላክን አዩት ! ሙሴ ኤልያስ
አባቱም አለ ! ልጄን ስሙት
ቃሌ ነውና ! የወለለድኩት
ድምጽህን ሰማና በብሩህ ደመና
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣና።

አዝ

ክብር አርሞንየም ያልታየባቸው
ቅዱስ ተራራ ስምህ ደስ አላቸው
ሰላም ሰላም የታቦር ተራራ
ብርሀነ መለኮት አንቺ ላይ አበራ

አዝ

በተዋሕዶ ወልድ የከበረው
የእግዚአብሔር አብ ልጅ ወልደ ማርያም ነው
ቡሄ በሉ ቡሄ በሉ
የአዳም ልጆች ብርሀንን ተቀበሉ

አዝ

አባቴ ቤት አለኝ ለከት
እናቴም >> >> >>
አጎቴም >> >> >>
አክስቴም >> >> >>

አዝ

የአመት ልምዳችን ከጥንት የመጣ
ከተከመረው ከመሶብ ይውጣ
ከደብረታቦር ጌታ ስለመጣ
የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ

አዝ

ኢትዮጵያውያን ያሪክ ያላችሁ
ባህላችሁን ያዙ አጥብቃችሁ
ችቦውን አብሩ እንደ አባቶቻችሁ

አዝ

ቡሄ /

የደብረ ታቦር በዓል በምዕመናን ዘንድ ቡሄ ( ) ይባላል :: የሁኔታና የድርጊት አፈጻጸም ገላጭ የሆነው የዚህ ስያሜ መሠረተ ቃል በልዩ ልዩ አስተያየት ሲብራራ ይገኛል :: ይኸውም :-

ቡሄ :- የበራ የደመቀ የጎላ ብርሃን የብርሀን በዓል ማለት ነው :: በሌላም በኩል ዳቦቴ (ዳቦት የችቦ ስም ነው ) ችቦዬ መብራቴ ማለት ነው (አዲሱ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ 95 እና 234)

ቦኽየ :- ማለት ተገለጠ , ነጣ , በራ ሆነ ማለት ነው :: ራሰ በራን ሰው ቡሃ ራስ እንዲሉት :: (በታቦር ተራራ የጌታ ገጹ እንደጸሃይ ማብራቱን ለማጠቀስ )

ቡሔ :- ማለት ደግሞ ደስታ ፍስሐ ማለት ይሆናል :; (ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል መዝ 88  12)

በሓ :- ማለት የሰላምና የቡራኬ ቃል ሲሆን ፍስሓ ሰላም ማለት ይሆናል ::

ብሔ :- - በእብራይስጥ ቁዋንቁዋ አምላክ ማለት ነው :: ይህ ቃል ከጊዜ ብዛት ወደ ቡሔ የተለወጠ ይመስላል :;

ብሁዕ :- ማለት ያልቦካ ያልኮመጠጠ ማለት ነው ::

አከባበሩ

ችቦ ይበራል - መለኮታዊውን ብርሀን ለማመልከት

ሕብስቱ (ሙልሙል ዳቦው ) በታቦር ተራራ ዙሪያ ለነበሩት እርኞች ወላጆቻቸው ምግባቸውን ይዘው መሄዳቸውን ያመለክታል :: ጌታችን ብርሃነ መለኮቱ በገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እረኞች ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጡ፡፡ አሁን ታዲያ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የምናከብረውም ከዚህ በመነሣት ነው፡ አንድም ሕብስቱ ዮሐ 6  32-39 ላይ ያለውን ቃል ይጠቅሳል 

ጅራፉ ሲጮህ ማስደንገጡ ሦስቱ አዕማደ ሐዋርያት ማለትም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብ በድምጸ መለኮት መደንገጣቸውና መውደቃቸውን ያስታውሳል :: 

ዳግመኛም ወላጆች በታቦር ተራራ ዙሪያ የነበሩትን ልጆቻቸውን ለመፈለግ ችቦ እያበሩ ሲሄዱ ልጆቹም ጅራፍ በማጮህ ያሉበትን ስፍራ መጠቆማቸውን ያስረዳል ::

ዜማው

ሆያሆዬ  ሆያሆዬ 

ሆያ ሆዬ - ጌታዬ ሆይ እመቤቴ ሆይ እያሉ አባወራውን (እማወራዋን ) ማወደሳቸው ነው
 - ኦሆ በልዎ ለክርስቶስ (ያዕ 4  

እዚያ ማዶ ጭስ ይጨሳል  አጋፋሪ ይደግሳል
ያችን ድግስ ወጬ ውጬ  በድንክ አልጋ
ተገልብጬ
ያች ድንክ አልጋ  አመለኛ
ያለአንድ ሰው  አታስተኛ

አጋፋሪ - ቅዱስ ሚካኤል
ጭሱ - ደመና
ድግሱ - መና
ድንክ አልጋ - ምድረ ከነዓን

ይህም  40 ዓመቱ እሥራኤል ዘሥጋ ጉዞ መጋቤ ቅዱስ ሚካኤል ከፊት እየቀደመ ቀን ቀን በዓምደ ብርሃን ሌሊት ሌሊት ደሞ በእሳት እየመራ በደመና ዓይበት ቁዋጥሮ መና አውርዶ እያበላ , ውሀከጭንጫ አፍልቆ እያጠጣ ምድረ ርስትን እንዳወረሳቸው ያመለክታል ::

ያቸ ድንክ አልጋ አመለኛ ያለአንድ ሰው አታስተኛ መባሉም በክፉ ወሬ , በመጎምጀት , በአምልኮተ ጣዖት , በዝሙት , በሐሜት ከምድረ ግብጽ ከወጡት ግማሽ ሚሊዮን እስራኤላውያ መካከል ካሌብናእያሱ ብቻ ቅድስት ሀገርን መውረሳቸውን ያመለክታል ::

ይህን በመልአክ እጅ የተደረገውን መግቦተ እግዚአብሔር የሚያዘምሩት ልጆች በቅዱሳን ሐዋርያት , ታሪክል ከምስጠር ያስተባበርው ዜማቸውም በቃለ ስብከታቸው , ከየቤቱ የሚሰጣቸው ሙልሙልዳቦም ጌታችን ማቴ 10  5-11 ሲል ለስብከተ ወንጌል የተሰጣቸውን መመሪያ ያስታውሳል ::

ምንጭ :- የኢትዮጵያ  . . . ታሪክ

ባህላዊ በዓላችንን አክብረን የበዓሉ በረከት ተሳታፊዎች እንድንሆን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡



No comments:

Post a Comment